እስራኤል ሠለቸው
✦
እስራኤል ሰለቸው የሰማዩ መና፪
ዓለም አምሮት ሄደ ጸጋውን ተወና፪
የእግዚአብሔር ስጦታ ኅብስቱ ስልችቶት፪
ዓለም አምሮት ሄደ ከተወው ባርነት፪
የፈርኦን ጅራፍ አልታየው አለ
የእህል አምሮቱን ውርደቱን ከለለ፪
ግብፅ ልሄድ ብሎ አመጸ በእግዚአብሔር
መድርሱ አልገባውም ከከነዓን ሀገር፪
የኪዳኑ ታቦት የሙሴ ገጽታ
ዓለም ስላማረው አደረገው ተርታ ፪
የአምላክን ካህነት የአሮን ሥርዓት
በዓለም ለወጠው ትልቁን አምኃ፪
የኅብረቱን ጉዞ በፍቅር የሄደው
የማኅሌት ደስታ እስራኤል ታከተው፪
የእግዚአብሔርን ድንኳን ደመና ያጀባት
የኪዳኑን አርማ በበረሃ ተዋት፪
ዛሬም ይህ ትውልድ እስራኤልን ሆኗል
ቤክርስቲያኑን አምላኩን እረስቷል፪
ግብጽና ባቢሎን አጓጉተው ወስደውት
ወርቁን ከእጁ ጣለ መዳብ አስጎምጅቶት፪
የእግዚአብሔር ስጦታ ኅብስቱ ስልችቶት፪
ዓለም አምሮት ሄደ ከተወው ባርነት፪
የፈርኦን ጅራፍ አልታየው አለ
የእህል አምሮቱን ውርደቱን ከለለ፪
ግብፅ ልሄድ ብሎ አመጸ በእግዚአብሔር
መድርሱ አልገባውም ከከነዓን ሀገር፪
የኪዳኑ ታቦት የሙሴ ገጽታ
ዓለም ስላማረው አደረገው ተርታ ፪
የአምላክን ካህነት የአሮን ሥርዓት
በዓለም ለወጠው ትልቁን አምኃ፪
የኅብረቱን ጉዞ በፍቅር የሄደው
የማኅሌት ደስታ እስራኤል ታከተው፪
የእግዚአብሔርን ድንኳን ደመና ያጀባት
የኪዳኑን አርማ በበረሃ ተዋት፪
ዛሬም ይህ ትውልድ እስራኤልን ሆኗል
ቤክርስቲያኑን አምላኩን እረስቷል፪
ግብጽና ባቢሎን አጓጉተው ወስደውት
ወርቁን ከእጁ ጣለ መዳብ አስጎምጅቶት፪
✦