እቴ ሙሽራዬ
✦
እቴ ሙሽራዬ ሰሎሞን ያለሽ ፪
እኔም ልበልሽ እናቴ
እምአምላክ ግቢ በቤቴ
ሁሉም ሰው ለራሱ ወንበር ሲዘረጋ
ለክብር ሽልማት ራሱን ሲያስጠጋ
ድንግል እንደ ባርያ ውሃ ተሸክመሽ
ጌታን በትህትና ታገለግያለሽ
ነይ በደመና ፬
እመቤታችን ርኅርኂተ ኅሊና
እኔም ልበልሽ እናቴ
እምአምላክ ግቢ በቤቴ
ሁሉም ሰው ለራሱ ወንበር ሲዘረጋ
ለክብር ሽልማት ራሱን ሲያስጠጋ
ድንግል እንደ ባርያ ውሃ ተሸክመሽ
ጌታን በትህትና ታገለግያለሽ
ነይ በደመና ፬
እመቤታችን ርኅርኂተ ኅሊና
እቴ ሙሽራዬ ሰሎሞን ያለሽ ፪
እኔም ልበልሽ እናቴ
እምአምላክ ግቢ በቤቴ
እኔም ልበልሽ እናቴ
እምአምላክ ግቢ በቤቴ
ወርቀ ዘቦ ለብሰው በቤቱ ከሞሉት
በሐርና በእንቁ ከተንቆጠቆጡት
በሰው ፊት ያማሩ ብዙ ሆነው ሳለ
ጌታ ግን ወደደሽ እናቴ ነሽ አለ
ነይ በደመና ፬
እመቤታችን ርኅርኂተ ኅሊና
በሐርና በእንቁ ከተንቆጠቆጡት
በሰው ፊት ያማሩ ብዙ ሆነው ሳለ
ጌታ ግን ወደደሽ እናቴ ነሽ አለ
ነይ በደመና ፬
እመቤታችን ርኅርኂተ ኅሊና
እቴ ሙሽራዬ ሰሎሞን ያለሽ ፪
እኔም ልበልሽ እናቴ
እምአምላክ ግቢ በቤቴ
እኔም ልበልሽ እናቴ
እምአምላክ ግቢ በቤቴ
አሳድጎ ሳለ መልአኩ መግቦ
ተሸልመሽ ሳለ በዝቶልሽ ተዉቦ
እጅግ በትህትና ስላገለገልሽው
እንደ ኪሩብ መልአክ ጌታን ተሸከምሽው
ነይ በደመና ፬
እመቤታችን ርኅርኂተ ህሊና
ተሸልመሽ ሳለ በዝቶልሽ ተዉቦ
እጅግ በትህትና ስላገለገልሽው
እንደ ኪሩብ መልአክ ጌታን ተሸከምሽው
ነይ በደመና ፬
እመቤታችን ርኅርኂተ ህሊና
እቴ ሙሽራዬ ሰሎሞን ያለሽ ፪
እኔም ልበልሽ እናቴ
እምአምላክ ግቢ በቤቴ
እኔም ልበልሽ እናቴ
እምአምላክ ግቢ በቤቴ
የባርያውን ውርደት ተመልክቷልና
ለወለድሽው ንጉሥ ይድረሰው ምስጋና
ከልብ የወጣ እንጂ ከንቱውን አይደለም
ንጽሕት እንላለን እኛ ለዘለዓለም
ነይ በደመና ፬
እመቤታችን ርኅርኂተ ኅሊና
ለወለድሽው ንጉሥ ይድረሰው ምስጋና
ከልብ የወጣ እንጂ ከንቱውን አይደለም
ንጽሕት እንላለን እኛ ለዘለዓለም
ነይ በደመና ፬
እመቤታችን ርኅርኂተ ኅሊና
እቴ ሙሽራዬ ሰሎሞን ያለሽ ፪
እኔም ልበልሽ እናቴ
እምአምላክ ግቢ በቤቴ
እኔም ልበልሽ እናቴ
እምአምላክ ግቢ በቤቴ
✦