ዕፀ መስቀል

ዕፀ መስቀል የክብር መውረሻ
ሰይጣንን ድል መንሻ
የክብር ባለቤት ዕፀ መስቀል የተሠዋበት ዕፀ መስቀል
ዕፀ መስቀሉ ነው ዕፀ መስቀል የዓለም መድኃኒት ዕፀ መስቀል
አዝ . . .
እንደ እሌኒ ንግሥት ዕፀ መስቀል ፍጹም አክብራችሁ ዕፀ መስቀል
ሁላችሁ ገስግሱ ዕፀ መስቀል መስቀሉን ይዛችሁ ዕፀ መስቀል
አዝ . . .
ያለ ኃይለ መስቀል ዕፀ መስቀል የሰላም ዓርማችን ዕፀ መስቀል
ሊሸነፍ አይችልም ዕፀ መስቀል ሰይጣን ጠላችን ዕፀ መስቀል
አዝ . . .
እሳተ መለኮት ዕፀ መስቀል ያላቃጠለው ዕፀ መስቀል
ሰይጣንን የሚያነድ ዕፀ መስቀል ዕፀ መስቀሉ ነው ዕፀ መስቀል
አዝ . . .
እንደተባረከው ዕፀ መስቀል ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ ዕፀ መስቀል
በመስቀል ብርሃን ዕፀ መስቀል ወደ እውነት እንገስግስ ዕፀ መስቀል
አዝ . . .
የተዋሕዶ ልጆች ዕፀ መስቀል ገሥግሡ በተስፋ ዕፀ መስቀል
ዕፀ መስቀል ያዙ ዕፀ መስቀል ጠላት እንዲጠፋ ዕፀ መስቀል
አዝ . . .
← መዝሙር