ዕፁብ ድንቅ ሥራ

ዕፁብ ድንቅ ሥራ
በእውነት የታደለ የእግዚአብሔር ሙሽራ
በእውነት የታደለች የእግዚአብሔር ሙሽራ
ነፍሳችሁ በሰማይ ርግብ ትመስላለች
ከመላእክት ጋራ ዛሬ ዘምራለች
እልል በሉ ክርስቲያኖች ሁሉ
ያበራ ጀመረ ሙሽራው ፀዳሉ
ያበራ ጀመረ ሙሽሪት ፀዳሏ
ዕፁብ ድንቅ ሥራ
በእውነት የታደለ የእግዚአብሔር ሙሽራ
በእውነት የታደለች የእግዚአብሔር ሙሽራ
ከክርስቶስ ሰላም እንዴት ይርቃል ሰው
ሥጋና ደሙን ሳይሳሳ ከሰጠው
የመንፈስ ቅዱስ ህፃናት በመሆን
በሥጋ ወደሙ መቀደስ አለብን
ዕፁብ ድንቅ ሥራ
በእውነት የታደለ የእግዚአብሔር ሙሽራ
በእውነት የታደለች የእግዚአብሔር ሙሽራ
በእግዚአብሔር ተባርኮ የመኖር ምሥጢር
የዘለዓለም ሕይወት ይሰጣል ፍቅር
ሥጋውን ፍሪዳ ደሙን መጠጥ አርጎ
ሰጥቶናል ዐማኑኤል ሕይወቱን ለውጦ
← መዝሙር