እውነት በእውነት
✦
እውነት በእውነት ጌታ ተነስቷል
ተነስቷል በክብር ሞትን ድል አድርጓል
ተነስቷል በክብር ሞትን ድል አድርጓል
በሞቱ አጥፍቶ ሙስና መቃብር
የሙታን በኩር ሆኖ ተነስቷል ጌታችን፪
የሙታን በኩር ሆኖ ተነስቷል ጌታችን፪
እውነት በእውነት ጌታ ተነስቷል
ተነስቷል በክብር ሞትን ድል አድርጓል
ተነስቷል በክብር ሞትን ድል አድርጓል
ሳጥን ቢደረደር አፈር ቢረበረብ
ድንጋይ በድንጋይ ላይ ደግሞም ቢደራረብ
ምድር አልቻለችም አምላኳን ለመቅበር
ድንጋይ በድንጋይ ላይ ደግሞም ቢደራረብ
ምድር አልቻለችም አምላኳን ለመቅበር
እውነት በእውነት ጌታ ተነስቷል
ተነስቷል በክብር ሞትን ድል አድርጓል
ተነስቷል በክብር ሞትን ድል አድርጓል
የንጉሶች ንጉስ ሰማያዊ አንበሳ
ሞትን ድል አድርጎ በሰንበት ተነሣ፪
ሞትን ድል አድርጎ በሰንበት ተነሣ፪
እውነት በእውነት ጌታ ተነስቷል
ተነስቷል በክብር ሞትን ድል አድርጓል
ተነስቷል በክብር ሞትን ድል አድርጓል
ተቀደሰናል በጌታችን ደም
ፍቅሩንም የሰጠን እንደርሱ የለም
ሕያው ነው የሚኖር ለዘለዓለም
ፍቅሩንም የሰጠን እንደርሱ የለም
ሕያው ነው የሚኖር ለዘለዓለም
እውነት በእውነት ጌታ ተነስቷል
ተነስቷል በክብር ሞትን ድል አድርጓል
ተነስቷል በክብር ሞትን ድል አድርጓል
✦