እያለፈ ነው ዘመኔ
✦
እያለፈ ነው ዘመኔ ትእዛዙን ሳልፈጽም ወየው ለእኔ፪
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ ና ብሎ ወደእኔ፪
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለው ነይ ብሎ ወደ እኔ
በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ ብዙ አዝመራ፪
ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ ልኑር ከአንተ ጋራ፪
የማስብበት በየለእቱ ንጹሕ ልብን ስጠኝ አቤቱ ፪
ከትእዛዝህ ወጪ በመሆን እዳልቀር በከንቱ ፪
እንደየሥራው ለመስጠት በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ፪
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ ፊተናን የወጣ፪
እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ እየተማራችሁ ከቃሉ፪
ይመጣሉና በእርሱ ስም አምላክ ነን የሚሉ፪
ትእግሥትን በመያዝ ሁላችሁ እስከመጨረሻው ጠንክሩ፪
ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ የማዳን ተግባሩ፪
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ ና ብሎ ወደእኔ፪
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለው ነይ ብሎ ወደ እኔ
በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ ብዙ አዝመራ፪
ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ ልኑር ከአንተ ጋራ፪
የማስብበት በየለእቱ ንጹሕ ልብን ስጠኝ አቤቱ ፪
ከትእዛዝህ ወጪ በመሆን እዳልቀር በከንቱ ፪
እንደየሥራው ለመስጠት በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ፪
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ ፊተናን የወጣ፪
እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ እየተማራችሁ ከቃሉ፪
ይመጣሉና በእርሱ ስም አምላክ ነን የሚሉ፪
ትእግሥትን በመያዝ ሁላችሁ እስከመጨረሻው ጠንክሩ፪
ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ የማዳን ተግባሩ፪
✦