ፈቃዴ ይህ ነው

ፈቃዴ ይህ ነው የሠውን ነገር ላልናገር
የእኔ ተሽፍኖ ከቆምኩኝ በክብር
ፈቃዴ ይህ ነው የሰውን ነገር ላልናገር
ህይወቴ በሙሉ በኃጢአት ተመልታ
አምላኬ ከማረኝ በፍቅሩ ዝምታ
የሰው በደል ላላይ በእውነት ምያለው
እኔን ከታገሰኝ ፍቅር ተምሪያለው
ፈቃዴ ይህ ነው የሠውን ነገር ላልናገር
የእኔ ተሽፍኖ ከቆምኩኝ በክብር
ፈቃዴ ይህ ነው የሰውን ነገር ላልናገር
ባይኔ ፊት ተጋርዶ ያለውን ምሰሶ
እያየ ካለፈኝ በምህረት ታግሶ
የሰው ጉድፍ ላላይ በእውነት ምያለው
እኔን ከታገሰኝ ፍቅር ተምሪያለው
ፈቃዴ ይህ ነው የሠውን ነገር ላልናገር
የእኔ ተሽፍኖ ከቆምኩኝ በክብር
ፈቃዴ ይህ ነው የሰውን ነገር ላልናገር
አንተ ቀራጩ ሰው ያለህ አቀርቅረህ
በምህረት ተመለስክ ከኔ ይልቅ ድነህ
ባንተ ላይ ስጠቁም የኔን ጸሎት ትቼ
የመዳኑ ሰዓት አለፉ ቀኖቼ
ፈቃዴ ይህ ነው የሠውን ነገር ላልናገር
የእኔ ተሽፍኖ ከቆምኩኝ በክብር
ፈቃዴ ይህ ነው የሰውን ነገር ላልናገር
← መዝሙር