ፈራሁ

ቀኑ ከረፈደ ከመሸብኝ መጣው
ደጃፍህ ላይ ቆምኩኝ እንዳልገባ ፈራው
በደሌን ሳትመዝን ግባ ብትለኝም
ሀጥያቴ ከበደኝ #አላራመደኝም (2x)
የሰው እድሜውኮ አጭር ነው ጥቂት ነው
እንዴት ነው ሳላውቅህ ዘመኔ ያለቀው
ጉብዝናዬን አለም ስቃ ተጫውታበት
እንዴት ብዬ ልርገጥ ደጅህን በድፍረት
ፈራሁኝ ልገባ ወይ አልገባ
እንዴት ይመዘናል ያንተ ደም በእኔ እንባ (2x)
እኔ ፈራሁ እንጂ አንተ እኮ አታስፈራም
መምጣቴ ነው ደስታ ፍቅርህ አይታማም
ሽምቅቅ አለች ነፍሴ መስቀልህን ሳየው
በደሌን አስብኩት ደምህን እያየው
ፈራሁኝ ልገባ ወይ አልገባ
እንዴት ይመዘናል ያንተ ደም በእኔ እንባ (2x)
በንፅህና ፊት እንዴት እቆማለሁ
እንደ መላእክቱ በምን ጋርዳለውሁ
እራሴን መሸፈኛ ክንፈ የለኝም እኔ
ይታያል ሀጥያቴ የበደል እርቃኔ
ፈራሁኝ ልገባ ወይ አልገባ
እንዴት ይመዘናል ያንተ ደም በእኔ እንባ (2x)
ጠዋት እና ማታ ለመጣው አንድ ነው
አምሽቶ ለገባው እኩል ትከፍላለህ
አብረሃም ወይ ይስሃቅ በድንኳንህ ቢያድሩ
በአንተ መንግሥት ግን ከወንበዴ አይቀደሙም
ፈራሁኝ ልገባ ወይ አልገባ
እንዴት ይመዘናል ያንተ ደም በእኔ እንባ (፪ኅ)
← መዝሙር