ፈተና ቢገጥማት

ፈተና ቢገጥማት ቅድስት አፎሚያ
ሚካኤል ብላ ስትጣራ
ፈጥኖ አዳናት ከጭንቅ ከመከራ
ነውና እምነቷ ጽኑ ነው ምግባሯ
ሚካኤል መጣላት ተአምሩን ሊሠራ
ለአፎሚያ ታምሩን ሊሰራ
አዝ
ፍጡነ ረድኤት መጣና ገስግሶ
እንደ ኃያልነቱ ኃይሉን አፈራርሶ
በመጣበት አስኬደው መልሶ
አዝ
በእምነት ስንጠራው ጸንተን በሃይማኖት
ቶሎ ይደርድልናል ፍጡነ ረድኤት
ሚካኤል ሊቀ መላእክት
አዝ
ኃያሉ ሚካኤል ተራዳኢው መልአክ
ምሕረት እንዲሰጠን
ለምንልን ከአምላክ
ሚካኤል ሀገራችንን ባርክ
አዝ
← መዝሙር