ፍቅርህ ማረከኝ
✦
ፍቅርህ ማረከኝ በሕይወቴ በዘመኔ ፪
እግዚአብሔር ለኔ መድኃኒቴ
ፍቅርህ ማረከኝ በሕይወቴ በዘመኔ
-------------------
ተገዝቻለሁ በወርቅ ደምህ
ዓለምን ትቼ ላገለግልህ
ሞትህ ሕይወቴ ለነ ሆኖኛል
ባንተ መከራ ሸክሜ እርቋል
ለክብርህ ቆሜ እዘምራለሁ ፪
እንደ አቅሜ አገኝሃለሁ ፪
…አዝ…
ምድርና ሰማይ እልል ይበሉ
ምስጋናም ላንተ ይድረስ እያሉ
መሳይ የለህም ለቅድስናህ
አቀርባለሁኝ ላንተ ምስጋና
ጣቴ በገና ይደረድራል ፪
በቀን በሌሊት ያመሰግናል ፪
…አዝ…
ክብርህን አይተው ጠላቶች ፈሩ
ለጌትነትህ ወድቀው ተገዙ
እንዲህ ነህ አምላክ እንዲህ ነህ ጌታ
ሁሉን በፍቅር የምትረታ
ባንተ ተመካሁ በፈጣሪያችን ፪
አዳኝ በሆንከው በንጉሳችን ፪
…አዝ…
እግዚአብሔር ለኔ መድኃኒቴ
ፍቅርህ ማረከኝ በሕይወቴ በዘመኔ
-------------------
ተገዝቻለሁ በወርቅ ደምህ
ዓለምን ትቼ ላገለግልህ
ሞትህ ሕይወቴ ለነ ሆኖኛል
ባንተ መከራ ሸክሜ እርቋል
ለክብርህ ቆሜ እዘምራለሁ ፪
እንደ አቅሜ አገኝሃለሁ ፪
…አዝ…
ምድርና ሰማይ እልል ይበሉ
ምስጋናም ላንተ ይድረስ እያሉ
መሳይ የለህም ለቅድስናህ
አቀርባለሁኝ ላንተ ምስጋና
ጣቴ በገና ይደረድራል ፪
በቀን በሌሊት ያመሰግናል ፪
…አዝ…
ክብርህን አይተው ጠላቶች ፈሩ
ለጌትነትህ ወድቀው ተገዙ
እንዲህ ነህ አምላክ እንዲህ ነህ ጌታ
ሁሉን በፍቅር የምትረታ
ባንተ ተመካሁ በፈጣሪያችን ፪
አዳኝ በሆንከው በንጉሳችን ፪
…አዝ…
✦