ገብርኤል በሰማይ

ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤጥ በምድር
ይመሰክራሉ ድንግል ያንቺን ክብር
ትፀንሲ ሲልሽ በከበረ ዜና
ይሁንልኝ ያልሽው ትውልድ እንዲፅናና
ከገብርኤል ሰምተው መላእክቱ ሁሉ
ለበጉ ማደሪያ ክብርን ይሰጣሉ ።
ብፅዕት እንላለን እኛም አደግድገን
የራማውን ልዑል አብነት አድርገን
__ አዝ __
ስርሽ በምድር ነው ሀረግሽ በሰማይ
ንፁህ መሶበ ወርቅ የተመላሽ ሲሳይ
የማፀንሽ ፍሬን በላነው ጠጣነው
በኤፍራታ ሰምተን በዱር አግኝተነው
የተሰወረውን መና በልተነዋል
ከተመረጡትጋ ብፅዕት ብለናል ።
__ አዝ __
ከተፈጥሮ በላይ ጽንስን ያዘለለ
የእሳት ምሰሶ ባንቺ ተተከለ
የእግዚአብሄር ሃገሩ የእንጀራ ቤታችን
ምንኛ ድንቅ ነው ክብርሽ እናታችን ።
ብፅዕት እንላለን እኛም አደግድገን
ቅድስት ኤልሳቤትጥን አብነት አድርገን ።
__ አዝ __
ተወልዶ በግርግም ተኝቶ ስላዩት
ሰውና መላዕክት አብረው አከበሩት
የጥሉ ግድግዳ በልጅሽ ፈረሰ
በዳግምዊት ሔዋን የአዳም ዘር ተካሰ ፡፡
እጅ እንነሳለን ሆነን በትህትና
ክብርሽን መመስከር ክብራችን ነውና ።
ብርኤል በሰማይ ኤልሳቤጥ በምድር
ይመሰክራሉ ድንግል ያንቺን ክብር
← መዝሙር