ገና እንዘምራለን

ገና እንዘምራለን
እንደ መላእክቱ ብርሀንን ለብሰን
ገና እንዘምራለን
ወላዲተ አምላክን ከፊት አስቀድመን
በዳዊት በገና መሰንቆ ታጅበን
ለሥላሴ ክብር ገና እንዘምራለን::
ገና እንዘምራለን
አዝ........
በምሥጋና ሥርዓት ከሰለጠኑት ጋር
ልብን የሚመስጥ መዝሙር እየዘመርን
ያልተሰማ ዜማ ያልታየ ምስጋና
ይፈልቃል አይቀርም በእኛ ልቦና::
ገና እንዘምራለን
አዝ.........
በትዕቢት ሳይሆን በታላቅ ትህትና
በልዩ ተመስጦ በፍቅር ልቦና
ሥራችን ይሆናል ለአምላክ ምሥጋና::
ገና እንዘምራለን
አዝ........
ዳዊት በተመስጦ እርቃኑን ቢሆንም
ሜልኮል በዝማሬው ብትስቅበትም
አምላክን ወደደ እንዲያመሰግነው
በደስታ እንዳይዘምር ከልካዩ ሰው ማነው::
ገና እንዘምራለን
← መዝሙር