ጌታ ሆይ እባክህ

ጌታ ሆይ እባክህ እንለምንሃለን
በፍቅር በደስታ እንድንኖር አድርገን
ጌታ ሆይ እባክህ --በኃጢአት ብንወድቅም
ምንም ብንበድልህ
መዓትህ የራቀ
ብዙ ነው ምሕረትህ
ጌታ ሆይ እባክህ አንተ ኃብታችን ነህ
የራስ ዘውዳችን
ውስጣችን የምትኖር
የማትለየን
ጌታ ሆይ እባክህ እንለምንሃለን
በፍቅር በደስታ እንድንኖር አድርገን
ጌታ ሆይ እባክህ --- አንተ ካልሰራኸው
ትዳር ጎጆውን
በከንቱ መድከም ነው
መልፋት መባዘን
ጌታ ሆይ እባክህ በቅዱስ ፈቃድህ
ሁሉን ትሰራለህ
የጀመርከውን ቤት
ታከናውናለህ
ጌታ ሆይ እባክህ እንለምንሃለን
በፍቅር በደስታ እንድንኖር አድርገን
ጌታ ሆይ እባክህ --- እንድትሰጠን ለእኛ
የዕለት እንጀራችንን
ምግበ ሥጋንና
ጌታ ሆይ እባክህ ምግበ ነፍሳችንን
ከሰይጣን ፈተና
ከፀብ ከክርክር
አምላክ ሆይ ሠውረን
ጠብቀን ዘወትር
ጌታ ሆይ እባክህ እንለምንሃለን
በፍቅር በደስታ እንድንኖር አድርገን
← መዝሙር