ጌታ ሆይ ውለታህ

ጌታ ሆይ ውለታህ ተአምርህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው
በሐዋርያት አድረህ ብዙ መክረኸኛል
ስለ ኃጢያቴ ሞተህ ሕይወት ሰጥተኸኛል
ጌታ ሆይ ውለታህ ተአምርህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው
ጌታ ሆይ ውለታህ ታምርህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው
ከኀዘኔ ፈጥነህ ደርሰህ አረጋጋኸኝ
አይዞህ ልጄ ብለህ ስወድቅ አነሳኸኝ
ከማይጠፋው እሳት ከሞት ያወጣኸኝ
ለአንተ የምከፍለው ምን ስጦታ አለኝ
ጌታ ሆይ ውለታህ ታምርህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው
እውነተኛ ረዳት አምላኬ አንተ ነህ
ጌታ ሆይ ከእናት ልጅ እጅግ ትበልጣለህ
መታመን በአንተ ነው ደግሞም መመካት
ወቅት የማይለውጥህ የማታውቅ ወረት
ጌታ ሆይ ውለታህ ታምርህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው
ሰምህ ምግብ ሆኖ ስጠራህ እጠግባለሁ
ፍቅርህን ለብሼ ፍጹም እረካለሁ
በሰማይ በምድር በነፍስም በሥጋ
በአንተ እመካለሁ አልፋና ዖሜጋ
← መዝሙር