ጌታ ሆይ

ጌታ ሆይ አይሁድ አማጽያን ሰቀሉህ ወይ
የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ
የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመሰቀል
የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት
ንጹሕ ክርስቶስ ሆነ ወንጀለኛ ብለህኛ ስለእኛ
መሰቀል አሸክመው አስረው ገፈፉህ እያዳፉህ
እጅና እግርህን በብረት ተመታ የዓለም ጌታ
የሾህ አክሊል ደፍተህ ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ
ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው
ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ
በመሰቀል ላይ ተጠማሁ ስትል ታላቅ በደል
ሀሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው
ይቅር ባይ ግልጽ በደላችንን ሁሉ ሳታይ
አንተ ቅር በለን በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ
← መዝሙር