ጌታ ተነስቷል

ጌታ ተነስቷል
ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ
===========
ጌታ ተነስቷል እልል እልል በሉ
አምላክ ተነስቷል የምስራች በሉ
ሙስና መቃብር በኃይሉ አጥፍቶ
ሁላችን አየነው ክርስቶስ ተነስቶ
አዝ---------------------//
አዳምን ለማዳን ቃል ኪዳን ገብቶለት
ዘመኑን ጠብቆ ካሣ ሊከፍልለት
ከሰማያት ወርዶ የተሰ ቀለ ው
ሞትን በሞት ሽሮ ይኸው አየነው
አዝ---------------------//
ደቀ መዛሙርቱ እጅጉን ተጨንቀው
በጌታቸው መሞት በኃዘ ን ተመተው
በተዘጋ ደጃፍ ተሰብስበው ሳለ
እጆቹን ዘርግቶ ሰላም ለእናንተ አለ
አዝ---------------------//
ማርያም መግደላዊት እየገሰገሰች
በሌሊት ተነስታ ወደ አምላኳ ሄደች
አይሁድ አንገላተው የሰቀሉት ጌታ
ተነስቶ አግኝታው ተመላች በደስታ
← መዝሙር