ግነዩ ለእግዚአብሔር

ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ሔር
አዝ--------------
እናመስግናሽ የአምላክ እናት በዝማሬ
የዓለም ቤዛ ነውና የማኅፀንሽ ፍሬ
አዝ -----------
ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከአንቺ ተወልዶ
መለኮት ወረደ ዮርዳኖስ እኛን ለመቀደስ
አዝ -----------
በድንግልና የወለድሽው ክርስቶስ
የድኩማኖች ብርታት ነው የሕሙማን ፈውስ
አዝ ------------
በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ እዳችንን ፋቀ
በቸርነቱ ጠብቆ ከበደል አራቀን
አዝ -------------
ስምሽን የጠራ ዝክርሽንም የዘከረ
ቅድስት ቅዱሳን ማርያም ድንግል አንቺ ነሽ
አዝ ----
እመቤታችን እናታችን ማርያም
የተማጸነሽ ይድናል ለዘለዓለም
አዝ ----
ድንልናሽ ሳይለወጥ ወልድን የወለድሽ
የጌታችን እናት ማርያም ድንግል ሆይ አንቺ ነሽ
የጌታችን እናት ማርያም ንጽሕት ሆይ አንቺ ነሽ
ድንግልናሽ ሳይለወጥ ወልድን የወለድሽ
የጌታችን እናት ማርያም ድንግል ሆይ አንቺ ነሽ
የጌታችን እናት ማርያም ንጽሕት ሆይ አንቺ ነሽ
← መዝሙር