ጊዜዬ እስኪደርስ
✦
ጊዜዬ እስኪደርስ ወደአንተ መምጫዬ
ለንሰሓ አብቃኝ አቤቱ ጌታዬ አቤቱ ጌታዬ
ብርሃኔ መድኃኒቴ ተስፋህ ይመልሰኝ
ጥፋቴን ደምስሰህ ይቅርታ አድርግልኝ
ተስፋዬ እረዳቴ አንተ አትጣለኝ
አምላኬ አታጥፋኝ ከሲኦል አድነኝ
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
መሐሪ ይቅር ባይ ምሕረትህ ይጎብኘኝ
ከኃጢአት ፍላጻ ጸጋህ ይታደገኝ
አዳኜ መድኃኒቴ ሰላምን ላክልኝ
የድኅነት ደጆችህን በፍቅር ክፈትልኝ
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
አቤቱ ምሕረትህ በእኔ ላይ ይሁን
ተጨነኩ ጌታዬ ስጠኝ ሰላምን
ከክፉ እንድሸሽ አድነኝ እኔን
በጎ እንድሠራ ምራኝ መንገዱን
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
ሕይወት ሞት ድኅነት መኖራቸውን ባምንም
ኃጢአት ውድቀት ጥፋት አያዘናጋኝም
ሥርየት እንደማገኝ ተስፋ ቢኖረኝም
ትምክህቴ አንተ ነህ በሌላ አልመካም
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
የበደሌ ብዛት የሚያስከፋም ቢሆን
በሥጋ በደምህ እጠብ ኃጢአቴን
ወዳንተ እመጣለሁ አደራ ነፍሴን
በሰማያዊ ቤት አኑር ሕይወቴን
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
ለንሰሓ አብቃኝ አቤቱ ጌታዬ አቤቱ ጌታዬ
ብርሃኔ መድኃኒቴ ተስፋህ ይመልሰኝ
ጥፋቴን ደምስሰህ ይቅርታ አድርግልኝ
ተስፋዬ እረዳቴ አንተ አትጣለኝ
አምላኬ አታጥፋኝ ከሲኦል አድነኝ
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
መሐሪ ይቅር ባይ ምሕረትህ ይጎብኘኝ
ከኃጢአት ፍላጻ ጸጋህ ይታደገኝ
አዳኜ መድኃኒቴ ሰላምን ላክልኝ
የድኅነት ደጆችህን በፍቅር ክፈትልኝ
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
አቤቱ ምሕረትህ በእኔ ላይ ይሁን
ተጨነኩ ጌታዬ ስጠኝ ሰላምን
ከክፉ እንድሸሽ አድነኝ እኔን
በጎ እንድሠራ ምራኝ መንገዱን
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
ሕይወት ሞት ድኅነት መኖራቸውን ባምንም
ኃጢአት ውድቀት ጥፋት አያዘናጋኝም
ሥርየት እንደማገኝ ተስፋ ቢኖረኝም
ትምክህቴ አንተ ነህ በሌላ አልመካም
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
የበደሌ ብዛት የሚያስከፋም ቢሆን
በሥጋ በደምህ እጠብ ኃጢአቴን
ወዳንተ እመጣለሁ አደራ ነፍሴን
በሰማያዊ ቤት አኑር ሕይወቴን
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
✦