ኃዲጎ ተስአ
✦
ኃዲጎ ተስአ ወተሰአተ ነገድ ፪
ማዕከለ ባህር፪ ቆመ ማዕከለ ባህር ፪
ማዕከለ ባህር፪ ቆመ ማዕከለ ባህር ፪
ጌታችን ተጠምቆ በዮሐንስ እጅ
የኃጢአትን ደብዳቤ ቀደደ በአዋጅ
ባህረ ዮርዳኖስ መቆም ተስኗት
ሸሸች ወደዋላ ከመለኮት ፊት
የኃጢአትን ደብዳቤ ቀደደ በአዋጅ
ባህረ ዮርዳኖስ መቆም ተስኗት
ሸሸች ወደዋላ ከመለኮት ፊት
ኃዲጎ ተስአ ወተሰአተ ነገድ ፪
ማዕከለ ባህር፪ ቆመ ማዕከለ ባህር፪
ማዕከለ ባህር፪ ቆመ ማዕከለ ባህር፪
ቀላያት ዘለሉ እፅዋት ዘመሩ
አንደበት አገኙ ግዑዛን አወሩ
የልጁን ጌትነት ክብሩንም ሊያስረዳ
በደመና መጣ አብም ተሰናዳ
አንደበት አገኙ ግዑዛን አወሩ
የልጁን ጌትነት ክብሩንም ሊያስረዳ
በደመና መጣ አብም ተሰናዳ
ኃዲጎ ተስአ ወተሰአተ ነገድ ፪
ማዕከለ ባህር ፪ ቆመ ማዕከለ ባህር ፪
ማዕከለ ባህር ፪ ቆመ ማዕከለ ባህር ፪
ከወደላይ መጣ ምስጢር ያለው ቃል
የምወደው ልጄን እርሱን ስሙት ሲል
አደለን ዳግመኛ ሁለተኛ ልደት
ከጎኑ በወጣው በማየ ሕይወት ጥምቀት
የምወደው ልጄን እርሱን ስሙት ሲል
አደለን ዳግመኛ ሁለተኛ ልደት
ከጎኑ በወጣው በማየ ሕይወት ጥምቀት
ኃዲጎ ተስአ ወተሰአተ ነገድ ፪
ማዕከለ ባህር፪ ቆመ ማዕከለ ባህር ፪
ማዕከለ ባህር፪ ቆመ ማዕከለ ባህር ፪
ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ
በዮርዳኖስ ቆመ አምላክ በአትቶ
ማድነቅ ይገባናል የውኃን ሥርዓት
በዓሉ ዛሬ ነዉ ቃናና ጥምቀት
በዮርዳኖስ ቆመ አምላክ በአትቶ
ማድነቅ ይገባናል የውኃን ሥርዓት
በዓሉ ዛሬ ነዉ ቃናና ጥምቀት
✦