ሃሌ ሉያ ለእርሱ

ሃሌ ሉያ ለእርሱ እንዘምር በእልልታ
ክብር ይገባዋል ለሠራዊት ጌታ
ክብር ይገባዋል ለሠራዊት ጌታ
ጸናጽል ከበሮ በገናም ይደርደር
ነፃ ላደረገን ከባርነት ቀንበር
ለፍቅር ለሰላም ለምሕረት አባት
ይጎሰም ነጋሪት ይነፋ መለከት
አዝ
ሁሉ በእጁ ሳለ ደኃ ለሆነልን
የነገሥታት ንጉሥ ጌታችን ይመስገን
ለገዛልን ርስት በደሙ ለዋጀን
በመስቀል ተሰቅሎ በሞቱ ለአዳነን
አዝ
ስለኛ ደኅንነት ሀፍረትን ለናቀው
ለአማልከት አምላክ ምስጋና ይድረሰው
እኛ ክርስቲያኖች ሁላችንም ዛሬ
ለዓለም መድኃኒት እናቅርብ ዝማሬ
← መዝሙር