ኃጢአቴ በዛ

ኃጢአቴ በዛ እመቤቴ
ምሕረት ላኪልኝ ለሕይወቴ
የፈጣሪ እናት አዛኝት
በአንቺ ነው ማግኘት የጽድቅ ሕይወት
ከሲሑል አውጪኝ አዛኝት
የጻድቃን እናት እመቤት
ሰላማዊት ናት ሀገረ እግዚአብሔር
በአንቺ ነው መወጣት ከኃጢአት ቀንበር
የሚሰግዱልሸ ጻድቃን ሰማዕ ት
የሚላኩልሽ ቅዱሳን መላዕክት
ከእነርሱ ጋር ነይ እመቤቴ
እንዲ ረቀኝ ሰማያዊው አባቴ
አስ ርቂኝ እኔን ከልጅሽ
እማልዳለው ከፊትሸ
ስምሽን ጠርቶ ያፈረ ማነው
የአዳም ተሰፋ ስራሽ ድንቅ ነው
የፍቅር እናት እመቤ ችን
አስ ርቂን እኛን ከጌ ችን
ዘወትር ነይልን እናቴ ማርያም
ላንቺ ቅርብ ነው መድኃኔዓለም
← መዝሙር