ኃያል ነው እግዚአብሔር

ኃያል ነው እግዚአብሔር
ኃያል ነው እግዚአብሔር
ኃያል ነው ቅዱሱ
//
አይቻለሁ በዓይኔ ሲቆም ማዕበሉ
አይቻለሁ በዓይኔ ሲታዘዝ ነፋሱ
//
ሰረገላውን በእሳት ሠርቶታል
በደመና ላይ ይረማመዳል
በብርሃን ድንኳን በሰማይ ያለው
እርሱ ነው ጌታ የምናመልከው
//
እውነት በፊቱ ፍትሕ በእጁ
ሲኦልም ገነት አሉ በደጁ
ሥልጣን የእርሱ ነው አለቅነት
ማን እንደ ጌታ ከአማልክት
//
ታቦር ተራራ ተንቀጠቀጠ
ግርማው ሲገለጥ ሁሉ ቀለጠ
ድንቅን አድራጊ ተአምረኛ
ከማዳኑ ጋር ይምጣ ወደ እኛ
//
ምድር ጠፈሩ ታዟል ለእርሱ
እሳት ተፈትሎ ሆኗል ቀሚሱ
የክብርህ ብርሃን ይብራ በልቤ
አንተ ነህ ለእኔ ውድ ገንዘቤ
← መዝሙር