ኃይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ
✦
ኃይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ፪
የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ ፪
የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ ፪
ተመረጠች ነፍሴ አንተን ለማወደስ
ከላይ ከአርያም ከሥላሴ መቅደስ
በአንድነት ሦስትነት በዙፋኑ ሞልቶ
የሚሳነው የለም ለሥላሴ ከቶ
ከላይ ከአርያም ከሥላሴ መቅደስ
በአንድነት ሦስትነት በዙፋኑ ሞልቶ
የሚሳነው የለም ለሥላሴ ከቶ
ኃይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ፪
የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ ፪
የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ ፪
ከመንገድ ዳር ልቁም የወደቀ ላንሳ
የተራበ ላብላ የታመመ አልርሳ
እንደ አብርሀም አርገኝ እንደ ደጉ አባት
ቤቴ እንዲሞላ ባንተ በረከት
የተራበ ላብላ የታመመ አልርሳ
እንደ አብርሀም አርገኝ እንደ ደጉ አባት
ቤቴ እንዲሞላ ባንተ በረከት
ኃይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ፪
የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ ፪
የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ ፪
ጠፈሩን በውሃ በጥበብ የሠራ
እኔስ ይገርመኛል የስላሴ ሥራ
ኑና ተመልከቱ ታምራት ሲሠራ
ሰዎች እልል በሉ ወላድ ሆነች ሳራ
እኔስ ይገርመኛል የስላሴ ሥራ
ኑና ተመልከቱ ታምራት ሲሠራ
ሰዎች እልል በሉ ወላድ ሆነች ሳራ
ኃይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ፪
የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ ፪
የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ ፪
አብ አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ወዶናል
ወልድ በተዋህዶ እኛንም መስሎናል
ኃይሉ ተገለጠ የመንፈስ ቅዱስ
በቅዱሳን አድሮ ሲያድን ሲፈውስ
ወልድ በተዋህዶ እኛንም መስሎናል
ኃይሉ ተገለጠ የመንፈስ ቅዱስ
በቅዱሳን አድሮ ሲያድን ሲፈውስ
ኃይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ፪
የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ ፪
የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ ፪
✦