ኃይልን በሚሠጠኝ

ኃይልን በሚሠጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ
ፈተና ቢገጠግመኝ ለበጎ ነው ብዬ አልፋለሁ
በሠንሠለት አስረው በወኅኒ ቢጥሉኝ
መከራን አብዝተው እጅግ ቢያስጨንቁኝ
ለበጎ ነው ብዬ ተስፋ አድርጌሃለሁ
ይሁን አንተ ያልከው እገዛልሃለሁ
አዝ ---
ትናንትናም ዛሬም አንተ ያው አንተነህ
ፍቅርህ አይቀየር ወረትም የለብህ
ስምህን መጥራቴ ሞገስ ይሆነኛል
ጠላቴ ቢፎክር መቼ ያሸንፈኛል
አዝ ---
በመከራው ብዛት ጉልበቴ ደከመ
ትካዜ ከብዶኛል ተስፋዬም ጨለመ
ነገር ቢሆን ባይሆን አንተን እንዳከብር
አድለኝ በጸጋ ጌታ የአንተን ፍቅር
አዝ ---
ከሀገር ተጥቼ በዱር መሠደዴ
በባእዳን ሀገር ርቄ መሄዴ
ለበጎ ነውና መቼ ይከፋኛል
ፈጽሞ እንዳልጠፋ ፍቅርህ ይይዘኛል
አዝ ---
← መዝሙር