ሐመልማል ሐመልማል
✦
ሐመልማል ፫ ወርቅ
ልብሱ የኛ ሙሽራ
ሐመልማለ ወርቅ
ልብሱ የኛ ሙሽራ
ሐመልማለ ወርቅ
በባቢሎን ምድር ያልተፈተለ ነው
በቤተመቅደሱ ሲለብሱት ያየነው
በክብር ካባው ላይ ጸጋው ተጨምሮ
ሞላቸው ሞገሱ በላያቸው አድሮ
በቤተመቅደሱ ሲለብሱት ያየነው
በክብር ካባው ላይ ጸጋው ተጨምሮ
ሞላቸው ሞገሱ በላያቸው አድሮ
ሐመልማል ፫ ወርቅ
ልብሱ የኛ ሙሽራ
ሐመልማለ ወርቅ
ልብሱ የኛ ሙሽራ
ሐመልማለ ወርቅ
የሙሽራው ጠረን መዓዛው ይስባል
በቅብዐ ሜሮን በዕጣኑ ከብሯል
ያንፀባርቃሉ እንደ አልማዝ ድንጋይ
በረከትን አፍስሰው ከምህረት እጁ ላይ
በቅብዐ ሜሮን በዕጣኑ ከብሯል
ያንፀባርቃሉ እንደ አልማዝ ድንጋይ
በረከትን አፍስሰው ከምህረት እጁ ላይ
ሐመልማል ፫ ወርቅ
ልብሱ የኛ ሙሽራ
ሐመልማለ ወርቅ
ልብሱ የኛ ሙሽራ
ሐመልማለ ወርቅ
በዚህ ዓለም ዕንቁ አልከበረም ዘርፉ
በፆም በፀሎት ነው ያማረው መርገፉ
የሰው እጅ አይደለም የተጠበበት
ከላይ የመጣ ነው ዕድፈት የሌለበት
በፆም በፀሎት ነው ያማረው መርገፉ
የሰው እጅ አይደለም የተጠበበት
ከላይ የመጣ ነው ዕድፈት የሌለበት
✦