ሐና እና ኢያቄም በስዕለት ያግኙሽ

ሐና እና ኢያቄም በስዕለት ያግኙሽ
ድንግል እናታችን በጣም ደስ ይበልሽ
በጣም ደስ ይበልሽ
ለመዳን ምክንያት የሆነችውን እናት
ንጽሕት ቅድስት እያልን እናመስግናት
እናመስግናት
ሐና እና ኢያቄም በስዕለት ያግኙሽ
ድንግል እናታችን በጣም ደስ ይበልሽ
በጣም ደስ ይበልሽ
ቤተ መቅደስ ኖርሽ በቅድስና
እየተመገብሽ ሰማያዊ መና
ሰማያዊ መና
ሐና እና ኢያቄም በስዕለት ያግኙሽ
ድንግል እናታችን በጣም ደስ ይበልሽ
በጣም ደስ ይበልሽ
ዕፁብ ነው ድንቅ ነው የአምላካችን ሥራ
የሰጠን ድንግልን እንዳናይ መከራ
እንዳናይ መከራ
← መዝሙር