ሐዋርያው
✦
ሐዋርያው መነኩሴ የመረጡት ሥላሴ፪
ተክለሃይማኖት ሆኗል ጠበቃ ለነፍሴ ፪
አዝ----------------
ዳሞት ይናገረው ያንተን ሐዋርያነት
የወንጌል ገበሬ የጣኦታት ጠላት
ጸሎተኛው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት
ክንፍን የተሸለምክ እንደ ሰማይ መላእከት ፪
አዝ ------------------
ብራናው ሲገለጽ ገድለ ተክለሃይናኖት
ከሰው ልጅ ልቡና ይወጣል አጋንንት
የቅዳሴው እጣን ሲወጣ ከዋሻው
ምድርን ይባርካል ጸሎቱ ምህላው፪
አዝ --------------
ከሱራፌል ተርታ ቆመህ በማጠንህ
ሥሉስ ቅዱስ እያልህ ስታመሰግን
ጸሎት ትሩፋትህ ትኅትና ስግደትህ
ጾምህ ከፍ አድርጎ ሰማይ አደረሠህ፪
አዝ -----------------
ዛፉ ሲመነገል አምላክ የተባለው
ሞቶሎሚ ሲያፍር ትልቅ ሰው ነኝ ያለው
የጻድቁ ጸሎት ብዙ ነው ምስጢሩ
ስድስት ክንፉ አወጣ ቢቆረጥ አንድ እግሩ ፪
አዝ ---------
የኢትዮጵያን ምድር አረስከው በመስቀል
ጭንጫው ፈራረሰ ተዘራበት ወንጌል
ትናንት የዘራኸው ዛሬም ለእኛ ሆንዋል
አምላከ ተክለ አብ ብለን ተምረናል
ተክለሃይማኖት ሆኗል ጠበቃ ለነፍሴ ፪
አዝ----------------
ዳሞት ይናገረው ያንተን ሐዋርያነት
የወንጌል ገበሬ የጣኦታት ጠላት
ጸሎተኛው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት
ክንፍን የተሸለምክ እንደ ሰማይ መላእከት ፪
አዝ ------------------
ብራናው ሲገለጽ ገድለ ተክለሃይናኖት
ከሰው ልጅ ልቡና ይወጣል አጋንንት
የቅዳሴው እጣን ሲወጣ ከዋሻው
ምድርን ይባርካል ጸሎቱ ምህላው፪
አዝ --------------
ከሱራፌል ተርታ ቆመህ በማጠንህ
ሥሉስ ቅዱስ እያልህ ስታመሰግን
ጸሎት ትሩፋትህ ትኅትና ስግደትህ
ጾምህ ከፍ አድርጎ ሰማይ አደረሠህ፪
አዝ -----------------
ዛፉ ሲመነገል አምላክ የተባለው
ሞቶሎሚ ሲያፍር ትልቅ ሰው ነኝ ያለው
የጻድቁ ጸሎት ብዙ ነው ምስጢሩ
ስድስት ክንፉ አወጣ ቢቆረጥ አንድ እግሩ ፪
አዝ ---------
የኢትዮጵያን ምድር አረስከው በመስቀል
ጭንጫው ፈራረሰ ተዘራበት ወንጌል
ትናንት የዘራኸው ዛሬም ለእኛ ሆንዋል
አምላከ ተክለ አብ ብለን ተምረናል
✦