ሀያል ነህ አንተ

ሀያል ነህ አንተ ሀያል፤
ደጉ መልአክ ገብርኤል
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት፤
አንተ ተራዳን በውነት
.
በዱራ ሜዳ ላይ #ገብርኤል
ጣኦት ተዘጋጅቶ #ገብርኤል
ሊያመልኩት ወደዱ #ገብርኤል
አዲስ አዋጅ ወቶ #ገብርኤል
ሲድራቅና ሚሳቅ አብድናጎም ፀኑ፤
ጣኦቱን እረግጠው በእግዚአብሄር አመኑ፤
.
አዝ
.
ተቆጣ ንጉሱ #ገብርኤል
በሶስቱ ህፃናት #ገብርኤል
ጨምሯቸው አለ #ገብርኤል
ወደ እቶን እሳት #ገብርኤል
ከሰማይ ተልኮ ወረደ መልአኩ፤
ከሞት አዳናቸው በእሳት ሳይነኩ፤
.
አዝ
.
ከእቶኑ ስር ሆነው #ገብርኤል
ዝማሬን ተሞሉ #ገብርኤል
ገፍተው የጣሏቸው #ገብርኤል
በእሳቱ ሲበሉ #ገብርኤል
አልተቃጠለችም የራሳቸው ፀጉር፥
አዩት መኩዋንንቱን የእግዚአብሄርን ክብር
.
አዝ
.
ናቡከደነፆር #ገብርኤል
እጁን ባፉ ጫነ #ገብርኤል
ሰለስቱ ደቂቅን #ገብርኤል
ከሳት ስላዳነ #ገብርኤል
ይክበር ጌታ አለ የላከው መላኩን፤
ሊያመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን!
← መዝሙር