ሐያል ነው

ሐያል ነው እርሱ ዘላለማዊ የሁሉ ጌታ
ሞትን የዋጠ ድልልን ያወጀ የማይረታ
ይሄው ተነሳ ደስ ይበለን 2x
ብርሃንን አየን
ይሄው ተነሳ ተነስቷል ጌታችን በእኩለ ሌሊት
ይሄው ተነሳ ሞትን ድል አድርጎ አለ በሰማያት
ይሄው ተነሳ የጨለማው ገዢ ስልጣኑ ተሻረ
ይሄው ተነሳ ሞቶ የነበረው ክርስቶ ከበረ
ይሄው ተነሳ የጠላት ሰራዊት ግብሩ ተገለጠ
ይሄው ተነሳ የዕዳ ፅፈታችን እንደስም ቀለጠ
ይሄው ተነሳ ሲኦል ባዶ ቀረ መዝጊያው ፈራረሰ
ይሄው ተነሳ ሲነሳ አምላካችን ሀይላችን ታደሰ
ይሄው ተነሳ በታላቅ ምስጋና በግሩም ውዳሴ
ይሄው ተነሳ ትንሳኤውን አይታ ተማርካለች ነፍሴ
ይሄው ተነሳ ብርቱነው ጠንካራ የተነገረለት
ይሄው ተነሳ ከእግዲ በኋላ ምን ስልጣን አለው ሞት
ይሄው ተነሳ እኛም ከእርሱ ጋራ ከሞት ተነስተናል
ይሄው ተነሳ በቤተ መቅደሱ ብርሃንን ለብሰናል
ይሄው ተነሳ ያአዳም ልጅ ሰንሰለት ቋጠሮው ተፈታ
ይሄው ተነሳ እጃችሁን አንሱ ዘምሩ በእልልታ
← መዝሙር