ሁለቱም አንድ ሆኑ ዛሬ
✦
ሁለቱም አንድ ሆኑ ዛሬ፪
በእግዚአብሔር በሕያው ቃሉ
ሁለቱም አንድ ሆኑ ዛሬ ፪
አዝ ---
በእግዚአብሔር በሕያው ቃሉ
ሁለቱም አንድ ሆኑ ዛሬ ፪
አዝ ---
ወንድና ሴት አድርጐ እንደፈጠራቸው
በኋላም በቃሉ አንድ አደረጋቸው
እናትና አባቱን የአዳም ልጅ ይተዋል
ከሚስቱ ጋር በሰላም በአንድ ይተባበራል
አዝ ---
ሁለቱም አንድ ሥጋ ሆነው ይኖራሉ
ብሎ አስተምሮናል ጌታችን በቃሉ
አንድ ሥጋ ናቸው አይደሉም ሁለት
የባልና የሚስት ሕይወት ወደፊት
አዝ ---
እንግዲህ እግዚአብሔር ካጣመራችሁ
በሆነው ባልሆነው ሰው አይለያችሁ
ለወገኖቻችሁ ምሣሌ ሆናችሁ
በክርስትና ፍቅር አምላክ ያኑራችሁ
አዝ ---
ምንጣፋችሁ ብሩህ መኝታችሁ ንጹህ
ስለሆነላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ
ዓለም እንዲደነቅ ሰይጣን እንዲያፍር
በሐዘን በደስታ ይኑራችሁ ፍቅር
አዝ ---
በኋላም በቃሉ አንድ አደረጋቸው
እናትና አባቱን የአዳም ልጅ ይተዋል
ከሚስቱ ጋር በሰላም በአንድ ይተባበራል
አዝ ---
ሁለቱም አንድ ሥጋ ሆነው ይኖራሉ
ብሎ አስተምሮናል ጌታችን በቃሉ
አንድ ሥጋ ናቸው አይደሉም ሁለት
የባልና የሚስት ሕይወት ወደፊት
አዝ ---
እንግዲህ እግዚአብሔር ካጣመራችሁ
በሆነው ባልሆነው ሰው አይለያችሁ
ለወገኖቻችሁ ምሣሌ ሆናችሁ
በክርስትና ፍቅር አምላክ ያኑራችሁ
አዝ ---
ምንጣፋችሁ ብሩህ መኝታችሁ ንጹህ
ስለሆነላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ
ዓለም እንዲደነቅ ሰይጣን እንዲያፍር
በሐዘን በደስታ ይኑራችሁ ፍቅር
አዝ ---
✦