ኢሳያስ በትንቢት
✦
ኢሳያስ በትንቢት እንደተናገረዉ
የድንግል ልዕልና እጅግ ከፍ ያለ ነዉ
የዘላለም ብርሀን አምላክ ስለሰጣት
ጨረቃም በለሊት ፀሀይም በመአልት
አያስፈልጓትም ለእርሷ ሊይበሩላት ፪
---
ፀሀይ ስለወጣ ከድንግል ተወልዶ፤
ብርሃን ለብሳለች ፍጹም ተዋህዶ።
ባንቺ ልዩ ፋና እንሄዳለን እንጅ፤
ድንግል እናታችን የዓለም አማላጅ።
--
የዘለዓለም ትምክህት ነሽና ድንግል ሆይ፤
የልጅ ልጅ ምልክት አርጎሻል አዶናይ።
ስምሽ ለዘላለም ይወሳል በፍቅር፤
ይጣፍጣል እና ከወተትም ከማር።
---
አምላክሽ እግዚአብሔር ብርሃንሽ ነውና፤
ገጽሽ ለዘልላለም ይኖራል ሲያበራ።
አባቶች በገዳም ጸሀይ አይፈልጉም፤
ዋሻቸው ያበራል በአዛኝቷ ማርያም።
ኢሳያስ በትንቢት እንደተናገረዉ
የድንግል ልዕልና እጅግ ከፍ ያለ ነዉ
የዘላለም ብርሀን አምላክ ስለሰጣት
ጨረቃም በለሊት ፀሀይም በመአልት
አያስፈልጓትም ለእርሷ ሊይበሩላት ፪
የድንግል ልዕልና እጅግ ከፍ ያለ ነዉ
የዘላለም ብርሀን አምላክ ስለሰጣት
ጨረቃም በለሊት ፀሀይም በመአልት
አያስፈልጓትም ለእርሷ ሊይበሩላት ፪
---
ፀሀይ ስለወጣ ከድንግል ተወልዶ፤
ብርሃን ለብሳለች ፍጹም ተዋህዶ።
ባንቺ ልዩ ፋና እንሄዳለን እንጅ፤
ድንግል እናታችን የዓለም አማላጅ።
--
የዘለዓለም ትምክህት ነሽና ድንግል ሆይ፤
የልጅ ልጅ ምልክት አርጎሻል አዶናይ።
ስምሽ ለዘላለም ይወሳል በፍቅር፤
ይጣፍጣል እና ከወተትም ከማር።
---
አምላክሽ እግዚአብሔር ብርሃንሽ ነውና፤
ገጽሽ ለዘልላለም ይኖራል ሲያበራ።
አባቶች በገዳም ጸሀይ አይፈልጉም፤
ዋሻቸው ያበራል በአዛኝቷ ማርያም።
ኢሳያስ በትንቢት እንደተናገረዉ
የድንግል ልዕልና እጅግ ከፍ ያለ ነዉ
የዘላለም ብርሀን አምላክ ስለሰጣት
ጨረቃም በለሊት ፀሀይም በመአልት
አያስፈልጓትም ለእርሷ ሊይበሩላት ፪
✦