ኢየሱስም አለ
✦
ኢየሱስም አለ ሐዋርያትን ጠርቶ
ሥርዓት ሊያስተምራቸው ከሁሉ ለይቶ
ይህን የአዲስ ኪዳን የፍቅር ስጦታ
ታላቅ ሰንሰለት ነው እጅግ የበረታ
ሥጋዬንም ብሉ ደሜንም ጠጡት
ስለሚሰጣችሁ የእውነት ሕይወት
ሂዱና አዘጋጁ የፋሲካን መአድ
ይገባዋልና ንጹሕ በግ ሊታረድ
ደቀመዛሙርቱ ጴጥሮስና ዮሐንስ
በፍጥነት ተጓዙ እከተማው ድረስ
አዩና ማድጋ የተሸከመ ሰው
ከተማ ሲደርሱ ሄደው ተከትለው
እጅግ ተደሰተ የቤቱ ባለቤት
ጌታው ባዳራሹ ስለተገኘለት
ሥርዓት ሊያስተምራቸው ከሁሉ ለይቶ
ይህን የአዲስ ኪዳን የፍቅር ስጦታ
ታላቅ ሰንሰለት ነው እጅግ የበረታ
ሥጋዬንም ብሉ ደሜንም ጠጡት
ስለሚሰጣችሁ የእውነት ሕይወት
ሂዱና አዘጋጁ የፋሲካን መአድ
ይገባዋልና ንጹሕ በግ ሊታረድ
ደቀመዛሙርቱ ጴጥሮስና ዮሐንስ
በፍጥነት ተጓዙ እከተማው ድረስ
አዩና ማድጋ የተሸከመ ሰው
ከተማ ሲደርሱ ሄደው ተከትለው
እጅግ ተደሰተ የቤቱ ባለቤት
ጌታው ባዳራሹ ስለተገኘለት
ኢየሱስም አለ ሐዋርያትን ጠርቶ
ሥርዓት ሊያስተምራቸው ከሁሉ ለይቶ
ይህን የአዲስ ኪዳን የፍቅር ስጦታ
ታላቅ ሰንሰለት ነው እጅግ የበረታ
ሥጋዬንም ብሉ ደሜንም ጠጡት
ስለሚሰጣችሁ የእውነት ሕይወት
ሥርዓት ሊያስተምራቸው ከሁሉ ለይቶ
ይህን የአዲስ ኪዳን የፍቅር ስጦታ
ታላቅ ሰንሰለት ነው እጅግ የበረታ
ሥጋዬንም ብሉ ደሜንም ጠጡት
ስለሚሰጣችሁ የእውነት ሕይወት
ሰዓቱ ሲደርስ የተወሰነለት
ከመአድ ሊቀመጥ ተገኘ ከዚያ ቤት
የቤቱ ባለቤት እጅግ የታደለው
ስምዖን ነበረ ጌታን የጋበዘው
እጅግ እመኝ ነበር ከመከራ በፊት
ከመአድ ልቀመጥ ከእናንተ ጋር በእውነት
የእግዚአብሔር መንግሥት እስክትመጣ ድረስ
ከወይኑ አልጠጣም ከማዕዱም አልቀምስ
ከመአድ ሊቀመጥ ተገኘ ከዚያ ቤት
የቤቱ ባለቤት እጅግ የታደለው
ስምዖን ነበረ ጌታን የጋበዘው
እጅግ እመኝ ነበር ከመከራ በፊት
ከመአድ ልቀመጥ ከእናንተ ጋር በእውነት
የእግዚአብሔር መንግሥት እስክትመጣ ድረስ
ከወይኑ አልጠጣም ከማዕዱም አልቀምስ
ኢየሱስም አለ ሐዋርያትን ጠርቶ
ሥርዓት ሊያስተምራቸው ከሁሉ ለይቶ
ይህን የአዲስ ኪዳን የፍቅር ስጦታ
ታላቅ ሰንሰለት ነው እጅግ የበረታ
ሥጋዬንም ብሉ ደሜንም ጠጡት
ስለሚሰጣችሁ የእውነት ሕይወት
ሥርዓት ሊያስተምራቸው ከሁሉ ለይቶ
ይህን የአዲስ ኪዳን የፍቅር ስጦታ
ታላቅ ሰንሰለት ነው እጅግ የበረታ
ሥጋዬንም ብሉ ደሜንም ጠጡት
ስለሚሰጣችሁ የእውነት ሕይወት
ህብስቱንም ቆርሶ ባርኮ አደላቸው
ስለእናንተ የሚሰጥ ሥጋዬ ይሄ ነው
ወይኑንም ባረከ አንስቶ ሰጣቸው
ስለናንተ የሚፈስ ደሜ ይህ ነው አላቸው
ይህን የሐዲስ ኪዳን የፍቅር ስጦታ
ታላቅ ሰንሰለት ነው እጅግ የበረታ
ስጋዬንም ብሉ ደሜንም ጠጡት
ስለሚሰጣችሁ የእውነት ሕይወት
መዝሙርም ዘመሩ እጅግ የተዋበ
ጌታም እግር ሊያጥብ ውኃን አቀረበ
ጴጥሮስ ግን ፈጽሞ አታጥበኝም አለ
ትሁት ነበርና እየተቻኮለ
ስለእናንተ የሚሰጥ ሥጋዬ ይሄ ነው
ወይኑንም ባረከ አንስቶ ሰጣቸው
ስለናንተ የሚፈስ ደሜ ይህ ነው አላቸው
ይህን የሐዲስ ኪዳን የፍቅር ስጦታ
ታላቅ ሰንሰለት ነው እጅግ የበረታ
ስጋዬንም ብሉ ደሜንም ጠጡት
ስለሚሰጣችሁ የእውነት ሕይወት
መዝሙርም ዘመሩ እጅግ የተዋበ
ጌታም እግር ሊያጥብ ውኃን አቀረበ
ጴጥሮስ ግን ፈጽሞ አታጥበኝም አለ
ትሁት ነበርና እየተቻኮለ
ኢየሱስም አለ ሐዋርያትን ጠርቶ
ሥርዓት ሊያስተምራቸው ከሁሉ ለይቶ
ይህን የአዲስ ኪዳን የፍቅር ስጦታ
ታላቅ ሰንሰለት ነው እጅግ የበረታ
ሥጋዬንም ብሉ ደሜንም ጠጡት
ስለሚሰጣችሁ የእውነት ሕይወት
ሥርዓት ሊያስተምራቸው ከሁሉ ለይቶ
ይህን የአዲስ ኪዳን የፍቅር ስጦታ
ታላቅ ሰንሰለት ነው እጅግ የበረታ
ሥጋዬንም ብሉ ደሜንም ጠጡት
ስለሚሰጣችሁ የእውነት ሕይወት
እግርህን ካላጠብኩ ዛሬ በዚህ ምሽት
እጣክፍል የለህም ከኔ ጋራ በእውነት
እንዲህ ባለው ጊዜ ጴጥሮስ ደነገጠ
መላ ሰውነቱን ለመታጠብ ሰጠ
እኔ ጌታ ስሆን አምላክ የምከብር
እግራችሁን ሳጥብ ስኖር ከናንተ ጋር
ይህንን ምሳሌ ተከተሉ በፍቅር
የኔ ስጦታ ነው በትሕትና መኖር
እጣክፍል የለህም ከኔ ጋራ በእውነት
እንዲህ ባለው ጊዜ ጴጥሮስ ደነገጠ
መላ ሰውነቱን ለመታጠብ ሰጠ
እኔ ጌታ ስሆን አምላክ የምከብር
እግራችሁን ሳጥብ ስኖር ከናንተ ጋር
ይህንን ምሳሌ ተከተሉ በፍቅር
የኔ ስጦታ ነው በትሕትና መኖር
✦