ከፈጣሪ በታች

ከፈጣሪ በ ች ከፍጡራን በላይ
ማን አለ እንዳንቺ ድንግል ንፁህ በአለም ላይ
ኦ ድንግል ማርያም ዘላለም
መኩሪያ ነሽ መመኪያ
አምላክ ለማደሪያ መርጦ ያዘጋጀሽ
ጽዮን የተባለች ሀገር ድንግል ሆይ አንቺው ነሽ
በሐሳብሽ ድንግል ድንግል በስጋሽ
ከፍጥረ ት ሁሉ ላንቺ ምሣሌም የለሽ
ፍቅሩ ለዘላለም የማይጠገበው
ከስም ሁሉ በላይ ጣፋጭ ድንግል የአንቺ ስም ነው
በእዝራ መሰንቆ በዳዊት በገና
ይገባሻል ላንቺ ድንግል ሁልጊዜ ምስጋና
አዝ- - - - -
እስኪ ልያዝና ደጋፊ ምርኩዜን
እስኪ ልያዝና የረሃብ መድኃኒቴን
ወደ አምላኬ ቤት ልሄድ ልቀጥል ጉካዬን
አዝ - - - - - -
ለፍርድ ስጠራ በደለኛው እኔ
የእኔ መማጸኛ ድንግል ቁሚልኝ ከጎኔ
← መዝሙር