ከካራን ውጡ

ከጣራን ዉጡ ከነዓን ግቡ
ወደ ጽድቅ ሕይወት ዛሬ ቅረቡ
ካራን ጣዖት ነዉ የሚመለከዉ
የአሕዛብ ሀገር የሙት መንደር ነዉ
እንደአባታችን እንደ አብርሃም
ወገኖች ዉጡ ከካራን ዓለም
የግፍ እንጅራ ይብቃችሁና
ከካራን ዉጡ በአምላክ ጐዳና
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
የጣዖት ምስል ከሚሸጥበት
ዓለም በዝሙት ከሚነድበት
ከሰዶም መንደር ከካራ ዉጡ
የኃጢአትን ሰንሰል ዛሬ ቁረጡ
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
የኃጢአት ዓለም ዛሬ ይብቃና
የፍቅር ሕይወት እንልበስና
ከካራን መንደር በፍጥነት ወጥተን
ከነዓን ገብተን ማደር አለብን
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
ማርና ወተት ከሚፈልቅበት
ሰዎች በፍቅር ከሚኖሩበት
ከሰማያዊት ኢየሩሳሌም
ዛሬ ብንገባ እናገኛለን የአምላክን ሰላም
← መዝሙር