ከክርስቶስ ፍቅር
✦
ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ ማነዉ፪
መከራ ችግር ስቃይ ወይስ መራቆት ነዉ፪
አንፈራም አንሰጋም አንጠራጠርም፪
እግዚአብሔር ከኛ ጋራ ይኖራል ለዘለዓለም፪
በትጋት ተራምደን እንግባ በጠዋት፪
በደሙ መሥርቶ ከሠራልን ቤት፪
ከቶ የት ይገኛል እንዲህ ያለ ቤት፪
የዉኃ ግድግዳ የደም መሠረት፪
የዉኃ ግድግዳ የደም መሠረት፪
ይኸዉ እዚህ አለ የአማኑኤል ቤት፪
መከራ ችግር ስቃይ ወይስ መራቆት ነዉ፪
አንፈራም አንሰጋም አንጠራጠርም፪
እግዚአብሔር ከኛ ጋራ ይኖራል ለዘለዓለም፪
በትጋት ተራምደን እንግባ በጠዋት፪
በደሙ መሥርቶ ከሠራልን ቤት፪
ከቶ የት ይገኛል እንዲህ ያለ ቤት፪
የዉኃ ግድግዳ የደም መሠረት፪
የዉኃ ግድግዳ የደም መሠረት፪
ይኸዉ እዚህ አለ የአማኑኤል ቤት፪
✦