ከሊባኖስ

ከሊባኖስ ከሊባኖስ ከልጅሽ ጋር ነይ
እመ አዶናይ ከሊባኖስ ወደእኛ ነይ
ጥበቃሽ ዘወትር ከሊባኖስ
እንዳይለየኝ ››
በሔድኩበት ሁሉ ››
ማረፊያ ሁኚኝ ››
አዝ ---
እኔ ባሪያሽን ››
ድንግል አትርሺኝ ››
በጽድቅ ሠሌዳ ››
ስሜን ጻፊልኝ ››
አዝ ---
ነፍስና ስጋዬ ››
አደራ እልሻለሁ ››
በልጅሽ ጽኑ ፍቅር ››
ተማጽኜሻለሁ ››
በልጅሽ ጽኑ ፍቅር ››
ተማጽኜሻለሁ ››
አዝ ---
ከመሞት በፊት
ለንስሓ አብቂኝ
ለነፍሴ ማረፊያ
አዘጋጂልኝ
አዝ ---
ከአንበሶች መኖሪያ
ከነብሮች ተራራ
መጥተሸ አስደስቺኝ
እናቴ ሙሽራ
አዝ ---
የልብስሸ መዓዛ
የሊባኖስ ሽታ
ሮማን ናርዶስ ነው
እናቱ ለጌታ
አዝ ---
እመቤቴ ስልሽ
ስምሽን ስጠራ
ፈጥነሽ ድረሺልኝ
ከቅዱሳን ጋራ
ፈጥነሽ ድረሺልኝ
ከሚካኤል ጋራ
ፈጥነሽ ድረሺልኝ
ከገብርኤል ጋራ
ፈጥነሽ ደረሺልኝ
ከኡራኤል ጋራ
← መዝሙር