ከመላእክት ጋራ
✦
ከመላእክት ጋራ
ከመላእክት ጋራ ሲገለጽ በሰማይ፤
ፀንተን እንጠብቀው ክብሩን ሁሉ እንድናይ፤
በግርማ ሲመጣ ባስደንጋጭ ሁኔታ፤
ወዮልሽ ነፈሴ ሆይ ወዮ የዛን ለታ፤
እኸ ምስጋና ይድረስህ ሁል ጊዜ ጧት ማታ
ሃሌ ሃሌ ሉያ የሠራዊት ጌታ፡
ፀንተን እንጠብቀው ክብሩን ሁሉ እንድናይ፤
በግርማ ሲመጣ ባስደንጋጭ ሁኔታ፤
ወዮልሽ ነፈሴ ሆይ ወዮ የዛን ለታ፤
እኸ ምስጋና ይድረስህ ሁል ጊዜ ጧት ማታ
ሃሌ ሃሌ ሉያ የሠራዊት ጌታ፡
ሰማይና ምድር ከፊቱ ሲሸሹ፤
ወዴት ልግባ ይላል ትልቁ ትንሹ፤
ጻድቃን ሲደሰቱ የሃጥአን ፋንታ፤
ሆኖ ጠበቃቸው ልቅሶና ዋይታ፤
ወዴት ልግባ ይላል ትልቁ ትንሹ፤
ጻድቃን ሲደሰቱ የሃጥአን ፋንታ፤
ሆኖ ጠበቃቸው ልቅሶና ዋይታ፤
እኸ ምስጋና ይድረስህ ሁል ጊዜ ጧት ማታ፤
ሃሌ ሃሌ ሉያ የሠራዊት ጌታ፤
ስለማይታወቅ አምላክ አመጣጥህ፤
በመንፈስህ አፅናን ፀንተን እንጠብቅህ፤
ሰይጣን እንዳይገዛን በመንግሥት ቦታ፤
እግዚኦ ከልለን ከልቅሶ ከዋይታ።
ሃሌ ሃሌ ሉያ የሠራዊት ጌታ፤
ስለማይታወቅ አምላክ አመጣጥህ፤
በመንፈስህ አፅናን ፀንተን እንጠብቅህ፤
ሰይጣን እንዳይገዛን በመንግሥት ቦታ፤
እግዚኦ ከልለን ከልቅሶ ከዋይታ።
✦