ከነቢያት ሀገር

ከነቢያት ሀገር ኢየሩሳሌም
ከቅድስት አውራጃ በቤተልሔም
በጎል ተወለደ መድኃኔዓለም
አዝ-----
ለእኛ ቤዛ ሊሆን በበደልነው ፈንታ
ዛሬ ተወለደ ይገባል እልልታ
አዝ ---------------------
የነግሥታት ንጉሥ የነዳያን ሕይወት
ተጠቅልሎ ተኛ በጎለ እንስሳ
አዝ ---------------------
ትኅትናን ሊያስተምር በሕፃንነት
በከብቶች ማደሪያ ተኛ በበረት
አዝ ---------------------
ግኡዛን የሆኑ የማይናገሩ
እስትንፋሳቸውን እንስሳት ገበሩ
← መዝሙር