ከንቱ ነኝ

ከንቱ ነኝ የከንቱ ከንቱነኝ
ዋስትና መከታ እግዚአብሔር ካልሆነኝ
ተስፋ የሚሆነኝ ሕይወት የሚሰጠኝ
እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ አምላኬ
አ.ዝ---------------------------//
እኔ ንጉሥ ነበርኩ በክብር ያጌጥኩኝ
ሁሉን በምድር ላይ በጥበብ ፈጸምኩኝ
የዚህ ዓለም ደስታ ምንም አላዋጣኝ
በመጨረሻው ግን በሞት ተወሰድኩኝ
አ.ዝ---------------------------//
ከፀሐይቱ በታች አዲስ ነገር የለም
ሰዎች ይደክማሉ እስከ ዘለዓለም
ጥበብን ፍለጋ ደክሜ ነበረ
ሁሉም ከንቱ ሆኖ በመቃብር ቀረ
አ.ዝ---------------------------//
ከኔ አስቀድመው ከበሩ ሁሉ
አፈር ተጭኖባቸው ከመቃብር አሉ
እብደትና እውቀት ሁሉን ቀወቅኳቸው
ምንም ቋሚ የለም ሁሉም ከንቱ ናቸው
አ.ዝ---------------------------//
ልቤን የጣልኩበት ተስፋ የጣልኩበት
አልጨበጥ ብሎኝ አለሁኝ በጭንቀት
የጥበቡም ብዛት ለትካዜ ሰጠኝ
እኔ በዚህ ምድር ጐስቋላ ፍጥረተረ ነኝ
አ.ዝ---------------------------//
ልቤንም ፈተንኩት በደስታ ብዛት
የዚህንም ዓለም ለውጥ ጣዕሙን ቀመስኩት
ሳቅም በልቤ ውስጥ ይፍለቀለቅ ነበር
ሁሉም ከንቱ ሆነ ገባ ከመቃብር
← መዝሙር