ከሰዎች ማነው
✦
ከሰዎች ማነው እንደ እኔ ትእዛዝህን ሻሪ፪
ከአማልክትስ ማነው እንዳተ መሀሪ፪
ከአማልክትስ ማነው እንዳተ መሀሪ፪
የኃጢያት ሸክም ከብዶብኝ ሲያስጨንቀኝ
ጠላቶች ከብበው በኔ ላይ ስዝቱብኝ
ብቸኝነቴን አይተህ ስለደረስክልኝ
ተመስገን እንጂ ላንተ ሌላ ምን አለኝ
አዝ ---
በደሌን አይተህ በቅጽበት ያላጠፋኸኝ
እንደ ጥፋቴ በቁጣ ያልተበቀልከኝ
ቸር እና የዋህ አምላክ እንደ አንተ ማን ይገኝ፪
አዝ ---
እንደ ሕዝቅያስ ጸሎቴን አምላክ ስማኝ
እንደ ዳዊትም ልመናዬን ተቀበለኝ
በዘመኔ እኩሌታ አምላኬ አትውሰደኝ
ወሰን በሌላት ፍቅርህ ታግሰህ ጠብቀኝ
አዝ ---
ጠላቶች ከብበው በኔ ላይ ስዝቱብኝ
ብቸኝነቴን አይተህ ስለደረስክልኝ
ተመስገን እንጂ ላንተ ሌላ ምን አለኝ
አዝ ---
በደሌን አይተህ በቅጽበት ያላጠፋኸኝ
እንደ ጥፋቴ በቁጣ ያልተበቀልከኝ
ቸር እና የዋህ አምላክ እንደ አንተ ማን ይገኝ፪
አዝ ---
እንደ ሕዝቅያስ ጸሎቴን አምላክ ስማኝ
እንደ ዳዊትም ልመናዬን ተቀበለኝ
በዘመኔ እኩሌታ አምላኬ አትውሰደኝ
ወሰን በሌላት ፍቅርህ ታግሰህ ጠብቀኝ
አዝ ---
✦