ከወገኔ ጋራ

ከወገኔ ጋራ እዘምራለሁኝ
በደስታ በሐሴት ስሙን እጠራለሁኝ
ምግብና መጠጤ አምላኬ ነውና
ዘወትር አቀርባለሁ ለጌታ ምስጋና
አዝ ---
ሕዝቡ ተስብስቦ በቤተ ክርስቲያን
ሲዘምር ደስ ይላል በአንድነት ሆነን
በረከት የሞላው ዝማሬ ይገርማል
ከዕጣኑ ጋር ወደ ላይ ይወጣል
አዝ ---
ቀሳውስቱ ሌሊት ማኅሌት ሲያቀርቡ
ከመላእክት ጋራ ወረብ ሲወርቡ
ብርሃን ለብሰን በደሰታ ስንዘምር
ትዝታው ልዬ ነው ኅሊና ሲሠውር
አዝ ---
ራእይ ነውና ኑና ተመልከቱ
ሰዎች ሲዘምሩ እንደመላእክቱ
የጽጌው ዝማሬ የትንሣኤው ደስታ
ልዩ ዝማሬ ነው እዳንዳይመስለን ተርታ
አዝ ---
← መዝሙር