ክብረ ቅዱሳን

ክብረ ቅዱሳን ይእቴክብረ ቅዱን
ሙዳዬ መና ግሩም ሙዳዬ መና
የቅዱሳኑ ክብር ነሸና
እንሰጥሻለን ቅኔ ምስጋና
የወለድሽልን የህይወት መና
ዝናብ ያለብሽ ታናሽ ዳመና
ትህትና ልብስሽ ፍቅር ውበትሽ
ፅንስ ያዘልላል ሰላምታ ድምፅሽ
እሳቱን ወልደሽ እሳት ታቅፈሻል
ሳልዘምርልሽ መቼ ይመሻል
የፀሃይ መውጫ ምስራቅ ሆነሽ
ታላቁን ብርሃን አየንብሽ
አትጨልምም ህይወታችን
ልጅሽ እስካለ ፀሃያችን
ሰአሊነ ሰላም እለኪ
ተማህፀን በኪዳነኪ
ንኢ ርግቢያ ምስለወለዲኪ
ሰማይ ወምድር ያወድሱኪ
← መዝሙር