ኪዳነ ምህረት እናቴ ምስጢረኛ ጓዳዬ

ኪዳነ ምህረት እናቴ ምስጢረኛ ጓዳዬ
የጎደለኝን ታውቂያለሽ
ከአፌ ሳይወጣ ሳልነግርሽ
አዝ......
አልፏል መናኛው ኑሮ
ምልጃሽ ውኃውን ቀይሮ
መልካሙ ወይን ደረሰ
እንባዬ ባንቺ ታበሰ
አዝ.........
ልዘምር ልቁም ከፊትሽ
ልምጣ ልንበርከክ ለክብርሽ
ብርቅ ከሀገር ከቤቴ
ከቶ አልረሳሽም እናቴ
አዝ........
አልልም መቼ ነው ቀኑ
የኔ መጎብኛ ዘመኑ
እንደሚፈፀም አውቃለው
ሁሉን በጊዜው አያለው
አዝ........
የልቤን ችግር ላዋይሽ
ከስዕልሽ ፊት ቆሜ
እንባዬ ቀድሞ ዝም አልኩኝ
ሳልነግርሽ ስለምታውቂ
← መዝሙር