ኪዳነ ምሕረት እናቴ

ኪዳነ ምሕረት እናቴ አማልጅኝ እኔን ከልጅሽ
የፍቅር እናት ነሽና አማልጅኝ እኔን ከልጅሽ
የሰላም እናት ነሽና አስታርቂኝ እኔን ከልጅሽ
የተገለጠው ብርሃን ከምሥራቅ የተወለደ
በፍቅር ሰንሰለት ታስሮ አለምን ሁሉ አዳነ
አዝ
በረሃውን ባሰብኩት ጊዜ ያንን የአሸዋ ግለት
አንቺ ትንሽ ብላቴና ኸረ እንዴት ቻልሽው በእውነት
አዝ
ዝም ብዬ ይደንቀኛል የአምላክን ሥራ ሳስበበው
ምክንያት አንቺን አድርጎ ይህንን ዓለም አዳነው
← መዝሙር