ኪዳነ ምህረት ኪዳነ ኮነ

ኪዳነ ምህረት ኪዳነ ኮነ
ምህረት አግኝቷል ባንቺ የታመነ!!
>>>>>>>>>>>>>>>>>€>>>
በምድር በሰማይ ቃልኪዳንሽ ፀንቷል
#ማርያም እያለ እስረኛው ተፈቷል
በረከት ነሽ ክብሬም ሽልማቴ
ኪዳነ ምህረት ነይልኝ እናቴ
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
የራቁት ነፍሳት ወደአንቺ ቀርበዋል
እናትነትሽ አሁን ገብቷቸዋል
የጠላት ቁጣ አንዳችም አይሰራም
ስልሽ ሰምተናል #እናታችን #ማርያም
አዎን ይልሻል ፍጥረት ሁሉ #ማርያም
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
ላንቺ ያለኝ ፍቅር አንቺም ታውቂዋለሽ
ባላጋራዬን ትረችልኛለሽ
በእምነት እወጣለሁ በልጅሽ ታምኜ
ምን ያገኘኛል ካንቺ ጋራ ሁኜ
ምን ይገጥመኛል ካንቺ ጋራ ሁኜ
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
#ለኢትዮጵያ #ልጆች #ፍቅርን ለምኝልን
ለአለም ሰዎች ሰላም ማልጅልን
አንፈልግም ለጠብ ለዘላለም
ትቶት ይሄዳል ሁሉም ይህንን አለም
← መዝሙር