ክንድህን እጠፍ የሚልህ ማነው
✦
ክንድህን እጠፍ የሚልህ ማነው
ማዳህን ተው የሚልህ ማነው
ቢከፋቸውም አሳዳጆቼ
እስከ አሁን አለሁ ባንተ ጸንቼ
አዝ..........
ማለፌ ሲቀር ሕይወት ስሞላ
ሲያልፍ ከላዬ የሞቴ ጥላ
ለምን አዘኑ ሰዱቃውያኑ
ስለከፋቸው ላይቀር ማዳኑ
አዝ..........
በባህሩ ዳር ህመሜን ትቼ
አልጋዬን ባዝል ድኜ በርትቼ
በሰንበት ዳነ ማረው ብላችሁ
ያዳነን ይሙት ለምን አላችሁ
አዝ..........
ስምዖን ዞር በል ይከፈት በሩ
ይብቃ ሲምረኝ ማንጎራጎሩ
ሀጢያቴን ፈቅዶ ጌታ ከተወው
ምንህ ተጎዳ በእንባዬ ባጥበው
አዝ..........
በግንባሬ ላይ አይኔን ቢሰራ
ቢደባልቀኝ ከሚያዩት ጋራ
ፊታችሁ ባዘን ለምን ጠቆረ
ሁሉን ቻይ ጌታ ስለ ከበረ
አዝ..........
አትዝጉት ደጁን እንመላለስ
የተወደደው በእኛ ላይ ይንገስ
የምናቀርበው ለጌትነቱ
የከበረውን ይዘናል ሽቱ
ማዳህን ተው የሚልህ ማነው
ቢከፋቸውም አሳዳጆቼ
እስከ አሁን አለሁ ባንተ ጸንቼ
አዝ..........
ማለፌ ሲቀር ሕይወት ስሞላ
ሲያልፍ ከላዬ የሞቴ ጥላ
ለምን አዘኑ ሰዱቃውያኑ
ስለከፋቸው ላይቀር ማዳኑ
አዝ..........
በባህሩ ዳር ህመሜን ትቼ
አልጋዬን ባዝል ድኜ በርትቼ
በሰንበት ዳነ ማረው ብላችሁ
ያዳነን ይሙት ለምን አላችሁ
አዝ..........
ስምዖን ዞር በል ይከፈት በሩ
ይብቃ ሲምረኝ ማንጎራጎሩ
ሀጢያቴን ፈቅዶ ጌታ ከተወው
ምንህ ተጎዳ በእንባዬ ባጥበው
አዝ..........
በግንባሬ ላይ አይኔን ቢሰራ
ቢደባልቀኝ ከሚያዩት ጋራ
ፊታችሁ ባዘን ለምን ጠቆረ
ሁሉን ቻይ ጌታ ስለ ከበረ
አዝ..........
አትዝጉት ደጁን እንመላለስ
የተወደደው በእኛ ላይ ይንገስ
የምናቀርበው ለጌትነቱ
የከበረውን ይዘናል ሽቱ
✦