ላይቀር መሞት
✦
ላይቀር መሞት አፈር መልበስ መግባት ከመቃብር
መስሎኝ ቋሚ ይህ ሥጋዬ ለእርሱ ብቻ ስጥር
ግን ለነፍሴ ቀረ ማስታወሴ፪
ዘመን መቁጠር እለት ወራት ክረምትና በጋ
ሌትና ቀን ሲፈራረቅ ሲጨልም ሲነጋ
በማየቴ ይሆን መደሰቴ፪
ኸረ ወዲያ ወዲያልኝ ዋይ ይብላኝ ለነፍሴ
አድርጎኛል የኃጢአት ምንጭ ደካማው መንፈሴ
ላልኖር በዓለም ቆሜ ለዘለዓለም
መሐሪ አምላክ ለጋስ ጌታ ቸሩ ፈጣሪዬ
አንተ እኮ ነህ ለዘለዓለም ለእኔ መመኪያዬ
ይቅር በለኝ ምሕረትህ አይራቀኝ፪
መስሎኝ ቋሚ ይህ ሥጋዬ ለእርሱ ብቻ ስጥር
ግን ለነፍሴ ቀረ ማስታወሴ፪
ዘመን መቁጠር እለት ወራት ክረምትና በጋ
ሌትና ቀን ሲፈራረቅ ሲጨልም ሲነጋ
በማየቴ ይሆን መደሰቴ፪
ኸረ ወዲያ ወዲያልኝ ዋይ ይብላኝ ለነፍሴ
አድርጎኛል የኃጢአት ምንጭ ደካማው መንፈሴ
ላልኖር በዓለም ቆሜ ለዘለዓለም
መሐሪ አምላክ ለጋስ ጌታ ቸሩ ፈጣሪዬ
አንተ እኮ ነህ ለዘለዓለም ለእኔ መመኪያዬ
ይቅር በለኝ ምሕረትህ አይራቀኝ፪
✦