ለእኔስ ልዩ ናት

ለእኔስ ልዮ ነች ድንግል ማርያም
ለእኔስ ልዮ ነች እመብርሃን
ፈልጌ ለቷንቺ ምስጋና አላገኘሁም
ልቤ ሲያበቅል የኃጢአት አረም
ዉስጤ ሲሸፍት አልተወችኝም
ከቤተመቅደስ እጃእን ዘርግታ
ትጠራኛለች የእኔ መከታ
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
የሆዴን ሐዘን የልቤን ምሥጢር
እነግርሻለሁ አንድም ሳይቀር
የምትሸሽጊ የሕዝብን ኃጢአት
ለእኔስ ልዮ ነሽ ድንግል አዛኚት
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
ጣዕሙ ልዮ ነዉ ከቷንቺ ጋር መኖር
ድንግልን ይዤ መቼም አላፍር
ወደ ጽድቅ ሕይወት ትወስደኛለች
ድንግል ማርያም ለእኔ እናቴ እኮ ነች
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
በሐዘን ስሰበር ማንን እጠራለሁ
ዉስጤ ሲደማ ለማን እነግራለሁ
ከኃጢአት እድፍ ንጹሕ መሆኛዬ
አንቺ ነሽ ለእኔ የኔስ መጽናኛዬ
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
የኃጢአት ቁስል ያለቷንቺ አይጠግም
ልቤ ሳይፈቅድ በሕይወት አልኖርም
ከልጅሽ ሌላ ምደኅን የለኝም
ከጸሎት በቀር ፍጹም አልድንም
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
← መዝሙር