ለእኛ ብሎ ተንገላታ
✦
ለእኛ ብሎ ተንገላታ የሁላቸን ጌታ
አዳም ቅጠል በልቶ ባመጣው በሽታ፪
አምላክ ዋለ ቀራንዩ ለብሶ ከለሜዳ
አዳም ሕግ አፍርሶ በጎተተው እዳ፪
ለመስቀሉ ተሰለፈ እየተገረፈ
በእጽ ሊፈውሰው በእጽ ላይ አረፈ፪
አዳም ቅጠል በልቶ ባመጣው በሽታ፪
አምላክ ዋለ ቀራንዩ ለብሶ ከለሜዳ
አዳም ሕግ አፍርሶ በጎተተው እዳ፪
ለመስቀሉ ተሰለፈ እየተገረፈ
በእጽ ሊፈውሰው በእጽ ላይ አረፈ፪
ምንም በደል ሳይኖርበት የዓለም መድኃኒት
ፍዳን ተቀበለ ለሰው ልጆች ድኅነት፪
በመሬት ላይ ተንገላታ ሩኅሩኅ ጌታ
አዳም ቅጠል በልቶ ባመጣው በሽታ፪
ፍዳን ተቀበለ ለሰው ልጆች ድኅነት፪
በመሬት ላይ ተንገላታ ሩኅሩኅ ጌታ
አዳም ቅጠል በልቶ ባመጣው በሽታ፪
✦