ለእጸ መስቀሉ

ለዕፀ መስቀሉ እናቅርብ ምስጋና
ክርስቶስ በደሙ ቀድሶልና
ጎልጎ ሲኖር አፈር ተንተርሶ
ይኸው ተገኘልን በዕሌኒ ልቅሶ
አጋንንት አይቀርቡም ከሩቅ ይሸሻሉ
እኛ ስንባረክ በዕፀ መስቀሉ
አዝ . . .
ክርስቶስ በደሙ የቀደሰው መስቀል
ድል መንሻ ሆነልን የሰይጣንን ኃይል
በመስቀል ተሰቅሎ ደሙ ባይሆን ቤዛ
ወድቆ ይቀር ነበር አዳም እንደዋዛ
አዝ . . .
ብርሃን ነው ለዓለም የጌ መስቀል
የድሆች መጽናኛ የደካሞች ኃይል
አይሁድ ይክዱል የጌን መስቀል
ለምናምን ድነት የሚሆነን ኃይል
አዝ . . .
አምነው ለተጠጉ ለተከተሉት
መስቀል ፈውስ ነው ይሆናል ድነት
የዲያብሎስን ኃይል የምንመክትበት
መስቀል ነው ቤዛችን ዓለም የዳነበት
አዝ . . .
← መዝሙር